FOR BETTER OROMIA

ኦሮሙማ እና ኢትዮጵያዊነት

አደግ እያልኩ ስመጣ የነዚህን ሁለቱን ማንነቶች መገለጫዎችና ልዩነቶች ለማወቅ ያላሰለሰ ጥረት አደርግ ነበር። ኦሮሙማ ምንድን ነው? ኢትዮጵያዊነትስ? ኢትዮጵያዊ ለመሰኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ምንድን ናቸው? በኢትዮጵያዊነትና ኦሮሙማ መካከል ያለው ግንኙነትና ልዩነት ምንድን ነው? አብረው ሊጓዙ የሚችሉ ናቸው ወይንስ ይጋጫሉ? የሚሉትን ለማወቅ በተለያዩ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ኦሮሞዎችንና ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያኖችን እጠይቅ ነበር። ምንም እንኳን መልሳቸው አጥጋቢ ሆኖ ባላገኘውም፤ በመጠኑም ቢሆን መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ቁም ነገሮችን አግንቼበታለሁኝ።

በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ የማገኛቸው መልሶች ድፍንና ግልጽ ያልሆኑ ነበሩ። በኢትዮጵያዊነቴ ከምንም በላይ እኮራበታለሁ ብለው የሚክሯሩ ሰዎች ጭምር ስትጠይቃቸው ሲደነባበሩና አጥጋቢ መልስ ሳይሰጡ ዘለው ኢትዮጵያዊነት ማለት ወኔ ነው ፤ ጀግንነት ነው ፤ የሶስት ሺህ አመት ነጻነት ፤ የራሷ የጊዜ ቀመርና ፊደል ፤ የሰለሞን የሳባ… ፤ የጥቁር መመኪያ ፤ ባህል ነው (የማን?)፤ ወዘተ እያሉ ይዘረዝራሉ። እነዚህ ዝርዝሮች አብዛኛውን የሃገሪቱን ህዝቦች የማይገልጹ/የማይወክሉ ከመሆናቸውም በላይ ታሪካዊ ጭብጥ ያሌላቸውና እርስ በራስ የሚጣረሱ ናቸው። ኦሮሙማ ያደኩበት ስለሆነ ብዙም ማብራሪያ አያስፈልገኝም ነበር።

ታዲያ አንድ የኦሮሞ ልጅ ስለ ኢትዮጵያዊነት ምን እንደሚያስብ ማወቁ ለሃገራችን የወደ ፊት እጣ ፋንታ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አንድ እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ነገር ቢኖር ፤ አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ ለኢትዮጵያዊነት እዚህ ግባ የሚባል ስሜት የለውም። ጠንካራ ሊባል የምችል የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያላቸውም ከአምስት ፐርሰንት ላይበልጡ ይችላሉ። ይህ ለምን ሊሆን ቻለ የሚል ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ ነው። እንደ አንድ የኦሮሞ ተወላጅና የስሜቱ ተጋሪ ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠቱ ላይከብደኝ ይችላል። እናም ለዚህ መልስ ሊሆኑ የምችሉ አስር ነጥቦችን ከነ ምሳሌያቸው አስቀምጫለው:-

1- የሃበሻ ልሂቃን ተጽኖ

ለምሳሌ
ለአንድነት እንጂ ለእኩልነት ቦታ ያለመስጠት። እኩልነትን ጨቁኖው አንድነትን የሚፈልጉ ፥ የሌሎችን መብት መቀበሉ ቀርቶ መስማቱ እንኳን የሚያንገሸግሻቸው። ለጋራ ሸንተረሩ እንጂ ለህዝቡ ደንታ የለላቸው። የሌላዉን ባህል ፥ ታሪክ ፥ አኗኗር ማንቋሸሽ። ከሁሉም ይልቅ ነባሩን የኦሮሞ ህዝብ መጤና በቅርብ ጊዜ ፈልሶ ሀገሪቱን ያጥለቀለቀ ፤ ሀገር አልባ ህዝብ እንደሆነ ለማሳመን የሚጥሩ:: በዳብተራዎች ሲፈበረኩ የነበሩትን የጥላቻ ታሪኮች ዛሬም እንደመልካም ነገር ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለመጥቀስ የሚጣጣሩ። የራሳቸውን ቋንቋ የመላ አገሪቷ አድርጎ የሚያቀርቡ። በሌሎች ሕዝቦች ቋንቋዎች ማሾፍ ፥ ዝቅተኛ አድርጎ ማቅረብ። ለምሳሌ ቪኦኤ(VOA) በአፋን ኦሮሞ ለምን ዜና ያሰራጫል ብሎ በአሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ቡድኖች ነበሩ። በ21ኛው ክፍለ ዘመንም እንዲህ በጥላቻ የተሞሉና ቢቻላቸው ህዝቡን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ድንቁርና ለመምራት የሚጥሩ ጥቂት የማይባሉ የሃበሻ ልሂቃን…ወዘተ— የብዙሃኑ ዋና ምክኒያት ሊሆኑ ይችላል።
.

2- ኢትዮጵያዊነትን በሰሜን(ክርስቲያን ሴሜቲኮች) ባህልና ታሪክ ፥ አኗኗርና አመለካከት መግለጽ

መቼስ ይሄ እለት ተእለት የምናየው ነገር ነው ምሳሌዎቹን መዘርዘር ብዙም ላያስፍልግ ይችላል:: እስቲ ለዝህም አንድ ምሣሌ ጣል እናድርግ:-
-ዶሮ ወጥ የኦሮሞም ሆነ የሌላው የደቡብ ህዝብ የባህል ምግብ ሆኖ አያውቅም:: ከሰሜን ኢትዮጵያ በስተቀር አይዘወተርም:: በአማራው ባህል ግን አንድ ሴት ትዳር ስትይዝ እንደ ፈተና ከሚቀርብላት ጥያቄ ውስጥ አንዱ የዶሮን ብልት ለይታ ማውጣትን ነው:: ይሄ የአማራ ባህል ነው:: ይሄ የአማራ ባህል ሆኖ ሳለ የተቀሩት ህዞቦችን የሚወክል ባህል ተደርጎ የኢትዮጵያ የባህል ምግብ እየተባለ በተደጋጋሚ ይቀርባል (ይነገራል):: እዚህጋ እኔ ማለት የፈለኩት ዶሮ ወጥ አንዱ የኢትዮጵያ የባህል ምግብ እንጂ ሀገር አቀፋዊ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ነው:: የኦሮሞ የባህል ምግብ ሚጪራ (ጭኮ) ነው:: እያንዳንዱ ብሄር የራሱ የሆነ በትንሹ ለሶስት ሺህ አመታት የተጠቀመበት ባህል አለው::

በተመሳሳይ መልኩ የሰሜን የባህል አልባሳትና ጭፈራዎችን ሀገር አቀፋዊ አስመስሎ ማቅረብ :: ለምሳሌ በዚህ አገላለጽ የጎንደርና የትግራይ የባህል ጭፈራዎች የኢትዮጵያ የባህል ጭፈራዎች ናችው: የኦሮሞና የሌላው ግን የብሄር ብሄረሰቦች::

3- ኢትዮጵያዊነትን ለመግለጽ የምንጠቀምባቸው ሀገራዊ ስይምቦሎች/Emblems/ ውስጥ ኦሮሞን/ ኦሮሙማን ያለማየት

ለምሳሌ
– ኦሮሞ ለብዙ ምዕተ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው (የገዳ ስርዓት) ባንዴራ ኢትዮጵያ በዛሬ ቅርጿ ስትፈጠር ታጠፎ እንዲቀመጥና የኦሮሞ ያልሆነውን አርንጓዴ: ቢጫ: ቀይ ባንዲራን በግድ የራሱ አድርጎ እንዲቀበል ተደርጓል።

-በተመሳሳይ መልኩ ኦሮሞ የራሱ የጊዜ ቀመር (Astronomical Calendar) እያለው ኦሮሞን የሚወክል በማስመሰል በአቢሲኒያውያን የቀን አቆጣጠር ሚሊኒየም ተክብሯል። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የሃበሻ ልሂቃን ተሰባስብው ሚሊኒየም ለሚለው ቃል የአማርኛ ፊችውን አጥተው እንኳን የአፋን ኦሮሞን ቃል (በርኩሜ- Barkumee- የሚለውን) ላለመጠቀም፥ የላቲኑን (“ሚሊኒየም”) ወስደዋል።

-የሃገሪቱ የገንዘብ ኖት(ብር) ላይ ጭምር ይሆው ነገር ሲንጸባረቅ እናያለን። ለምሳሌ መቶ ብራችን ላይ የአክሱም ኃውልትን ሃምሳዉ ላይ የጎንደር (የፋሲለደስ ቤተመንግሥትን) ነው የምናየው። ታዲያ! አንድ ኦዳ ወይም ኦባገዳ የለው የግንዘብ ኖት አይታቹሃል? መቼስ ስልጣኔ ማለት ድንጋይ ማቆምና መፈልፈል ብቻ ነው እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ!

4. የኦሮሞ ደራሲያን/እስኮላሮች ፤ አርቲስቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጽእኖ

————————————
ይቀጥላል!

Source: https://www.facebook.com/mamitti.luke/posts/764424790317426

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: