FOR BETTER OROMIA

የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ

የታሪክ ምሁራን እንደሚያወሱት አስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካቸውና ባህላቸው በውጉ ካልተጠናላቸው ሕዝቦች መካከል የኦሮሞ ብሔር አንዱ ነው። ለዚህም ዋንኛ ምክንያት ተብሎ የሚታመነው በማንነቱ ላይ በገዥው መደብ ይደርስበት የነበረ ጭቆናና ግልፅ ተጽእኖ ሲሆን ይባስ ተብሎም ማንነቱን ለማጥፋት ሲሸረብ የነበረ ፖለቲካዊ ደባ እንደሆነም ይታወቃል።የገዥ መደብ ጻሃፊዎንች ለምዕተ- ዓመትና ለበለጠ ጊዜ የፅሑፍ ባህል የሌላቸውን የሃገሪቱን ህዝቦች ታሪክ-አልባ እንደሆኑ ለማሳመንና አልፎም በጠላትነት በመፈረጅ ጭምር ሲያዩአቸው እንደቆዩና በተጻራሪ መልኩ የራሳቸውን ማንነት አጉልተው የገዥ መደብ ብሔርን የበላይነት እንዲቀበሉ በግድ ሲጭኑባቸው እንደነበር አይካድም።

ከሁሉም የሚያስገርመው ነባሩን የኦሮሞ ህዝብ መጤና በቅርብ ጊዜ ፈልሶ ሀገሪቱን ያጥለቀለቀ ፤ ሀገር አልባ ህዝብ እንደሆነ ለማሳመን የዉሸት ታሪክ ሲፈበርኩና ይህንኑ እንደመልካም ነገር በየት/ቤት ሲያስተምሩ መቆየታቸው ይታወሳል። ይህም አንሶ የአቢሲኒያ ደብተራዎች ኦሮሞን እንደ ሰው ልጅ ፍጡር ሁሉ ላለማሰብ ኦሮሞ ከወንዝ የወጣ ነው ብለው አላዝነዋል:: እንደ ገዥው መደብ አመለካከትና እምነት የኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ ማለት ከሴም ሕዝቦች ታሪክ ወይንም ከሰሜን ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሴሜቲክ ሕዝቦች ታሪክ ያለፈ አልነበረም።

በመሆኑም እንደ ሀገሪቱ እውነተኛ ታሪክ : ባህል : ሃይማኖትና ቋንቋ ይቆጠር የነበረው ሁሉ የራሳቸው የሆነው ብቻ ነበር። ከዚህም የተነሳ ኦሮሞ እውነተኛ ታሪኩን ሌሎች እንዳይገነዘቡት ወይም በተሳሳተ መልኩ እንዲረዱት ሆኗል። የግድፈቱ አንድ ምንጭ የሚሆነው የታሪክ ማይማንና እንግዳ የሆኑት የደብተራዎች ጭፍን ሥራ ነው። እነዚህ ሰዎች በበኩላቸው የኦሮሞን ታሪክ ለመረዳት ፍላጎቱና ክህሎቱም የሌላቸው በመሆኑ ከዚህ አንፃር የፈጠሩት ችግር ነው። ባገኙት ዕድልና በነበራቸውም ትንሽ ዕውቀት በመጠቀምም እውነተኛው ታሪክ እንዳይጻፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ለብሔራቸውና ለራሳቸው የፖለቲካ የበላይነት ሲሉ የኦሮሞን ታሪክ ሲያጣምሙ ከርመዋል።

* * *

እስቲ ፈጽሞ ሊታመኑ የማይችሉ የደብተራዎችን ተረት በመተው ካሉ ተጨባጭ ማስረጃዎች እኚህን እንመልከት:-

1- ፍራ ማውሮ የተባለ የፖርቹጋል ሰው በ1430 ባወጣው ካርታ ከሃበሻ አገር በስተደቡብ ፤ ለአውሮፓውያን ሳይታወቅ የቆየውን፤ የኦሮሞ ህዝብን በአካባቢው መኖር በካርታ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ አሰፈረ። በዚህ ካርታ ላይ የጊቤ እና አዋሸ ወንዞች ከሞላ ጎደል ትክክለኛ በሆነ ስፍራ ላይ ተመልክተዋል። በተጨማሪም ይሄው ሰው በ1457 በስቀመጠው የአለም ካርታ ለይም የኦሮሞ ህዝብ የነበረበትን ቦታ ከአሁኑ ጋር ከሞላ ጎደል በተመሳሰይ ቦታ አስፍሮት አናገኛለን።

2- ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት እንደፃፉት ኢትዮጵያ በአብዛኛው የኩሽ ሀገር ናት። ስሙ ሳይቀር ግሪኮች ኢትዮጵያ ብለው የተረጎሙት በጥንት እብራይስጥ ኩሽ ይባል የነበረዉ ሲሆን ፤ ግሪኮች በግብፅ በነገሱ ዘመን ከግብጽ በስተደቡብ የሚገኙትን የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች ኢትዮጵያ ብሎ ይጠሩ እንደነበር ተግልጿል ፤ በተጨመሪም አብዛኛወቹ ኩሾች በኢትዮጵያ ዉስጥ እንደሚኖሩ በመጥቀስ ከነዚህም መሀከል ኦሮሞ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

3- ሊንች እና ሮቢንስ የሚባሉ ሁለት የዉጭ ምሁራን ሰሜናዊ ኬኒያ በተገኘዉ ጥንታዊ አምድ ላይ ከተጻፈዉ መረጃ በመነሳት ኦሮሞዎች በ300 B.C አካባቢ የራሳቸዉ የሆነ የቀን መቁጠሪያ እንደነበራቸዉ አረጋግጠዋል። ይህም ሕዝቡ በዚሁ ክልል ለመኖሩ አንዱ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

4- በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ ከግራኝ አህመድ ወረራ በፊት በአካባቢው ይኖር እንደነበር አያሌ ማስረጃዎች ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ:-

ሀ- በ8ኛውና በ10ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተሰሩ የኦሮሞ የአምልኮ እና የአቴቴ ቁሳቁሶች መንዝ ውስጥ ‘ጋ* ጉር’ በሚባል ቦታ በአርኪዮለጂስቶች ተገኝቶአል። ደብረ ሊባኖስ አካባቢ ክርስትናን በማስፋፋት የሚታወቁት አባ ሊባኖስ (በ1015) ተደብቀው ያስተምሩ የነበሩበት አካባቢ ገዢ ‘ሆራ’ የሚባል ሲሆን ፤ ስሙም የኦሮሞ መሆኑ ፤ በአካባቢው በወቅቱ ኦሮሞ ሕዝብ የነበረ መሆኑን የሚጠቁም ነው። እነዚህ ታሪኮች [History of the Oromo to the Sixteenth Century, OCTB, 2006,] በገጽ 47 እና 62 ተጽፎዉ ይገኟሉ:: ቢያንስ ቢይንስ በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኦሮሞ ማህበረሰቦች በሸዋ አካባቢ እንደነበሩና ወደ ኋላ ዘመናት ላይ በ14ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ ከፊሉ ሕዝብ በክርስቲያኑ መንግሥት ተገፍቶ ከኖረበት የሸዋ ክልል ፤ ማዕከሉ ወደ ደቡብ ከመገፋቱ በፊት የኦሮሞ ይዞታ የአባ ሙዳ (ቃሉ)፥ የኦሮሞ ሐይማኖትና ፖለቲካ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል እንደቆየና ዋና ዋና የሙዳ ሥፍራዎችም በዚሁ ሸዋ ዉስጥ እንደነበሩ አያሌ ማስረጃዎች አሉ። ነገር ግን የግዥ መደብ ታሪክ ጸሐፊዎች በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተካሄደው ተሐድሶና የኦሮሞ ህዝብን እንቅስቃሴ እንደ መጤና እንግዳ በመቁጠር [የኦሮሞ] ፍልሰት ወይም ወረራ ሲሉ ሲዘግቡ ቆይተዋል ነገር ግን የነበረው እንቅስቃሴ የገዥ መደብ ጸሐፊዎች ስደት ይበሉት እንጂ በዘመኑ የነበረው ሕዝቡ ወደነባር ቀኤው የመመለስ ሂደት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ለ- አለቃ ታዬ ፤ መራ ተክለ ሐይማኖት ስመ ፤ መንግሥቱ ዛጉዌ በነገሰ በአስር ዓመቱ በ930 ዓ.ም የኦሮሞ ሕዝብ በመኃከለኛና ምሥራቅ ኢትዮጵያ እንደተስፋፉ መጻፈቸው የኦሮሞ ሕዝብ ከግራኝ አህመድ በፊት አምስት መቶ ዓመታት በላይ ቀደም ብሎ ሰፍሮ ይኖር እንደነበር የሚጠቁም ነው። [ታዬ ገብረ ማርያም ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ (1959)]

ሐ- የአክሱም ሐውልቶችን በተመለከተ እ.ኤ.አ በ1830ዎቹ መጀመሪያ አካባቢውን ጎብኝቶ በወቅቱ ሲነገርና ሲታመንበት የነበርዉን ጀ. ሊዉስ ክራፕፍ እንደሚከተለው ግልጾ ነበር። “ሃበሾች እንደሚያምኑት የኖህ ሶስት ልጆች አለምን በሶስት አቅጣጫ ተከፋፍለው ለመኖርና በሰፈሩበት አገር መታሰቢያ የሚሆን ምሶሶ እንዲያቆሙ ፥ በዚህም መሠረት ሴም በእስያ፥ ያፌት በአዉሮፓ፥ ካም ደግሞ በአፍሪካ ይህንኑ የድንጋይ ዓምድ ለመትከል ተስማሙ”። በአክሱም የተተከለው ሃውልት የካም ሃውልት ነው። የኩሽ ወገኖች የአክሱም ሃውልትን ስለመስራታችው የተነገረው ስለመሆኑ ካሰፈረ በኋላ የአክሱምን ሃውልት ከኦሮሞ ህዝብ ጋር የሚያያይዝ ሃሣብም አስፍሮ ይገኛል። በተጨማሪም ፑልታክ የተባለ የታሪክ ተመራማሪ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ኦሮሞዎች በምስራቅ አፍሪካ ይገኙ እንደነበር ጠቁሟል።

በሌላም በኩል ፦በእስልምና ሃይማኖት መነሻ ዘመን ከአረብ ሃገር ተሰደው ወደ አክሱም ንጉስ ነጃሺ ሲመጡ ፥ ንጉሡ “አሸማ ፤ አሸማ” ብለው እንደተቀበሏቸው ይነገራል። “አሸማ” የአፋን ኦሮሞ ቃል መሆኑን ሌሎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ይህን ግምት ያጠናክራሉ። እነ ኤም ታማሲዮ እና ኮምብ የተባሉ ፈረሳዊያን በ1830 ያሳተሙት የንጉስ ነጃሺ ደብዳቤ ትርጉም ላይ ይኸው አሸማ የሚለው ቃል የአፋን ኦሮሞ ሠላምታ መሆኑን ያረጋግጣል።

መ- የኦሮሞ ህዝብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከሌላው ክፍለ ዓለም ወደ ምሥራቅ አፍሪካ መጣ የሚባለው ታሪክ የፈጠራና መሠረታዊ ታሪካዊ ጭብጦችን የሚክድ ነው። ይህም ታሪክ በአቢሲኒያ የቤተመንግሥት ታሪክ ጸሓፍትና ደብተራዎች የመነጨ አፈታሪክ ነው። ምንም እንኳን የጥላቻ ዘመቻቸውን ከጻፉት ድብተራዎች እንደወረደ ገልብጠው ያስነበቡን ጥቂት ግራ የተጋቡ ስክላሮች ብኖሩም በአካባቢው ታሪክ ላይ በስፋት ያጠኑ የታሪክ ምሁራን ኦሮሞዎች የቅርብ ጊዜ መጠዎች ናቸው የሚለውን አመለካከት የማይቀበሉት መሆኑን በየጽሁፋቸው ገልጻዋል። በርካታ የታሪክ ምሁራን ከሀበሾች መምጣት አስቀድሞ (በፊት) ኦሮሞዎች በሰሜን ምሥራቅ የአህጉሩ ክፍል ይኖሩ እነደ ነበር አመልክተዋል።

እንደ ፐርሃም(1948) ገለጻ ፥ መጠዎች (ኢሚግራንት) የሴም ነገዶች (ሴማውያን) ወደ አህጉሩ በደረሱ ጊዜ በሰሜን ምሥራቅ የአህጉሩ ክፍል ፥ ምሥራቃውያን የሃም ዝርያዎች ማለትም ብዙ ጊዜ ኩሽ ተብለው የሚታወቁ ዝርያዎች ፥ ከነሱም ዉስጥ [ኦሮሞዎች]* የሚገኙበት ህዝቦች ይኖሩበት እንደ ነበር ገልጿል። ግሪንፊልድ (1965) የተባሉ የታሪክ ሊቃውንት [ኦሮሞዎች]* የቅርብ ጊዜ መጤዎች ናቸው የሚለውን አመለካከት የማይቀበሉት መሆኑን “Modern Ethiopia is a Product of the ‘Scramble’ በተሰኘው ጽሁፋቸው ላይ ግልጸዋል። እንዲሁም ፓንክረስት (1985) ከአቢሲኒያውያን በገዛራሳቸው ቃል ሲወርድ ሲዋረድ ከመጡ አፈታሪኮችና ወጎች ዉስጥ የሚክተለውን የላስታን አፈ-ታሪክ ጠቅሷል፦ “…የሰለሞን ልጅ የሆነው ምኒልክ በምሥራቅ በኩል አድርጎ ወደ አብሲኒያ ገባ። ይኸም አገር ከአዘቦና ከራያ [ኦሮሞዎች]* አገር ባሻገር ያለው ነው” -ከዚህም፦ ኦሮሞዎች በምኒልክ-አንደኛ ዘመን በአካባቢው እንደነበሩ በአቢሲኒያውያን ይታወቅ እንደ ነበር የሚጠቁም ነው።

ረ- ኦዳ ቡልቱም ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ፥ ለአያሌ መቶ አመታት የኦሮሞ ሐይማኖትና ፖለቲካ ማ ዕከል ሆኖ ሲያገለግል እንደነበር በትዉፊትና በጽሁፍ ሰነድ የሚገኙ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ስለ ኦዳ ቡልቱም በኢቱ ኦሮሞዎች ዘንድ ከሚነገሩ ትዉፊቶች ዉስጥ አንዱ ፦ ኦዳ ቡልቱም ለ810 ዓመታት የፖለቲካ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱ ይነገራል። እንዲሁም ኦዳ ቡልቱም ማዕከል ሆኖ ማገልል ከጀመረበት ወቅት አንስቶ እስከ ምኒልክ ወረራ ድረስ 64/ስድሳ አራት/ አባ ገዳዎች በተከታታይ ስልጣን እንደጨበጡ ይነገራል። ከጽሁፍ ሰነዶች ለማወቅ እንደሚቻለው አጼ ምኒልክ ሁለተኛ ፥ ሐረርን በወረራ የያዛት በ1887 ዓ.ም ነበር። ከዚህ አንጻር ኦዳ ቡልቱም ከ1887 በፊት ለ64 /ስድሳ አራት/ የገዳ ዘመን ማዕከል ሆኖ ቆይቷል ማለት ነው። ይህንን የገዳ ዘመን ፥ ወደ ፍጹማዊ የጊዜ አቆጣጠር ከቀየርን (አንድ ገዳ = 8 አመት) ፦ የኦዳ ቡልቱም ማ ዕከል የተመሰረተው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ2ኛው አጋማሽ ፥ ማለትም በ1375 አካባቢ ማለት ነው። ይህም ኦሮሞዎች ቢያንስ ለአንድ ምዕተ አመት ከአህመድ ግራኝ መስፋፋት በፈት በአካባቢው እንደ ነበሩ የሚያሳይ ነው።

ሰ- እንዲሁም በባሬንቱ ኦሮሞ ትውፊት ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ሲተላለፍ የቆየው ፦ የአባ ሙዳ(ቃሉ) መኖሪያ ሞርሞር (አባይ) እንደነበረና ይህም ይህም ከ200 ገዳ በፊት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሆኑ ይነገራል። የኦሮሞ የሃይማኖትና ፖለቲካ ማዕከል በመሆን ሞርሞር (አባይ) ለዘመናት ሲያገለግል እንደ ቆየና በኃላ በ1116 ዓ.ም በኦዳ ነቤ (ዱከም አካባቢ) “ሃሮምሳ ገዳ” (የገዳ መታደስ) ተከናወነ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኦዳ ነቤ የኦሮሞ ገዳ- የእምነትና የፖለቲካ- ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ሳለ ፥ የአባ ሙዳ መቀመጫ ወደ ኦዳ ሮባ (ባሌ- ጊኒር) በ1316 ዓ.ም የተዛወረ ሲሆን በመጨረሻም በመደ ወላቡ በ1450 (በአሁኑ ባሌ መደወላቡ ወረዳ) “ሃሮምሳ ገዳ” (የገዳ ተሃድሶ) ተካሄደ።

የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ በቅድሚያ ከመሃል ኢትዮጽያ ፥ ከሞርሞር (አባይ) ተነስቶ ፥ በኃላም ወደ ደቡብ ኢትዮጽያ አቅጣጫ እንደተጉዋዙና መደ ወላቡ ከደረሱ በኃላም ወደ ሰሜን ኢትዮጽያ አቅጣጫ መንቀሳቀሱን በማስረዳት የሚቀርበው ትንተና አሳማኝ ይመስላል።ይህም ትንተና የኦሮሞ የሃይማኖት ማዕከል የሆነው የአባሙዳ መቀመጫ ከአባይ ወይም ሞርሞር ተብሎ ከሚታወቀው አካባቢ ተነስቶ እስከ መደወላቡ ድረስ የመቀመጫ ለውጥ ማድረጉን መሰረት በማድረግ ነው።

ኦሮሞዎች በጋራ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በታሪክ ታዋቂ የሆኑ የእምነትና የፖለቲካ ማዕከላትና የሚገኙበት ሥፍራ(ቦታ)ና ጊዜ :-

‪#‎በከኒሳ_ራያ‬ —— በደቡብ ወሎና በሰሜን ሸዋ አከባቢ፤ ዘመኑ፦ ከረጅም ጊዜያት በፊት (ከክርስቶስ ልደት በፊት)
‪#‎ሪቡ_ፉጉግ‬ —— በደቡብ ወሎና በሰሜን ሸዋ አከባቢ፤ ዘመኑ፦ ከረጅም ጊዜያት በፊት (ከክርስቶስ ልደት በፊት)
‪#‎ከታ‬ ————- በግሼ (ሰሜን ሸዋ) አከባቢ፤ ዘመኑ፦ በ1ኛው ምዕተ ዓመት /ከክርስቶስ ልደት ወዲህ/
‪#‎ኦዳ_ነቤ‬ ——— ዱከም አካባቢ፤ ዘመኑ፦ ከ2ኛው እስከ 11ኛው ምዕተ ዓመት
‪#‎ኦዳ_ሮባ‬ ——— ባሌ (ባሌ- ጊኒር)፤ ከ12ኛው እስከ 14ኛው ምዕተ ዓመት
‪#‎መደ_ወላቡ‬ —– ባሌ፤ ከ1450- 1900 ባሉት ጊዜያት ዉስጥ ሆኖ ባሌ መደወላቡ ወረዳ ነው።

እነዚህ ሥፍራዎች የቃሉ መቀመጫዎችና አጠቃላይ የጎሳ ገዳ ተወካዮች ሸንጎ መቀመጫና እንዲሁም የገዳ ፌስቲቫሎች ሲካሄድባቸው የነበሩ አካባቢዎች ናቸው።

የኦሮሞ ሰንደቅ ዓላማ
*********************
የኦሮሞ ሰንደቅ ዓላማ
*********************
በኦሮሞ ታሪክና በጥንቱ የገዳ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የ"ቃሉ" -Qaallu- ተቋም ከፍተኛ ታሪክና ትልቅ ሥፍራ ያለው ነው። ይህ ተቋም ከፍተኛና ወሳኝ የሆነ የኦሮሞ ማሃበራዊ ባህልና የፖለቲካም ተቋም እንደ ሆነ ይገለጻል። እንዲሁም ለገዳ ክብረበዓላት ማከናወኛ ቁሳቁስ (ለምሳሌ እንደ ቦኩ ፤ በሄራዊ ሰንደቅ አላማ ላሉት) ግምጃ ቤት ሆኖ አገልግሏል። ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት የቃሉ ጥምጣም መለያ ቀለማትን የተከተሉ ናቸው። እሱም "ሱሪ ሩፋ" ይባላል - የቃሉ (መንፈሳዊ መሪ/የሃይማኖት አባት) ጥምጣም ማለት ነው። ይህ ብሄራዊ ባንዴራ ሥስት ቀለማት አሉት። ከላይ ጥቁር ፤ ከመሐል ቀይ፤ ከታች ነጭ ሆኖ ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ። በገዳ ሥርዓት የዕድሜ እርከኖች ውስጥ እነዚህ ሥስቱ ቀለማት ማለትም ጥቁር ፤ ቀይና ነጭ የሚወክሉት፥-

#ጥቁር - ሰርተው ለመኖር የደረሱትን (ፎሌ - ዶሪ)
#ቀይ - በመሥራት ላይ ያሉትንና (ሉባ)
#ነጭ - ደግሞ የሥራ አለሙ ውስጥ ያለፉትን የህብረተሰቡን መደቦች(ገዳሞጂ/ጉላ/ጃርሣ) ነው።

ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ በታዩት ለውጦች ምክኒያት ይህ ባንዴራ ተግባራዊ  እንዳይሆን ተከልክሏል።በኦሮሞ ታሪክና በጥንቱ የገዳ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የ”ቃሉ” -Qaalluu- ተቋም ከፍተኛ ታሪክና ትልቅ ሥፍራ ያለው ነው። ይህ ተቋም ከፍተኛና ወሳኝ የሆነ የኦሮሞ ማሃበራዊ ባህልና የፖለቲካም ተቋም እንደ ሆነ ይገለጻል። እንዲሁም ለገዳ ክብረበዓላት ማከናወኛ ቁሳቁስ (ለምሳሌ እንደ ቦኩ ፤ በሄራዊ ሰንደቅ አላማ ላሉት) ግምጃ ቤት ሆኖ አገልግሏል። ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት የቃሉ ጥምጣም መለያ ቀለማትን የተከተሉ ናቸው። እሱም “ሱሪ ሩፋ” ይባላል – የቃሉ (መንፈሳዊ መሪ/የሃይማኖት አባት) ጥምጣም ማለት ነው። ይህ ብሄራዊ ባንዴራ ሥስት ቀለማት አሉት። ከላይ ጥቁር ፤ ከመሐል ቀይ፤ ከታች ነጭ ሆኖ ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ። በገዳ ሥርዓት የዕድሜ እርከኖች ውስጥ እነዚህ ሥስቱ ቀለማት ማለትም ጥቁር ፤ ቀይና ነጭ የሚወክሉት፥-

‪#‎ጥቁር‬ – ሰርተው ለመኖር የደረሱትን (ፎሌ – ዶሪ)
‪#‎ቀይ‬ – በመሥራት ላይ ያሉትንና (ሉባ)
‪#‎ነጭ‬ – ደግሞ የሥራ አለሙ ውስጥ ያለፉትን የህብረተሰቡን መደቦች(ገዳሞጂ/ጉላ/ጃርሣ) ነው።

ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ በታዩት ለውጦች ምክኒያት ይህ ባንዴራ ተግባራዊ እንዳይሆን ተከልክሏል።

Leave a comment