ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየታየ ያለውን ያለመረጋጋት የቀሰቀሰው ተቃውሞ የሽብር አድራጎት ሳይሆን በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት የተፈቀደ፣ መዘዞቹ ደግሞ በሕግ አግባብ ሊታዩ የሚችል የተቃውሞ አቀራረብና መብትም ነው ሲሉ የሕግ አስተማሪና ተመራማሪው አቶ ፀጋዬ ረጋሳ ሃራርሳ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ከቪኦኤ ጽዮን ግርማ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ስላገርሸው ተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤ ከሕግ አኳያ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።የሕግ አስተማሪና ተመራማሪም ናቸው።
ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ክፍል ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡
http://amharic.voanews.com/audio/3109297.html
http://amharic.voanews.com/content/interview-with-tsegaye-regasa/3109310.html
Advertisements