FOR BETTER OROMIA

ወቅታዊ ጉዳይ

የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን  (2006-2030)

የጋራ ልማት ፕላኑ ከ2006 እስከ 2030 ዓ.ም. ድረስ የአዲስ አበባ ከተማን እና በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚገኙ ስድስት ከተሞችንና ስምንት የገጠር ወረዳዎችን የሚያካትት ነው፡፡ (ከነሱ መሀል ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ ገላን ይገኙበታል)፡፡

ፕላኑ ካካተታቸው የልማት ዘርፎች መካከል አካባቢና አረንጓዴ ማዕቀፍ፣ ከተማና የከተማ ዙሪያ ግብርና፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የማዕከላትና ገበያ ቦታዎች ዋና ዋና ግልጋሎቶች፣ ዋና ከተማ ማዕከል፣ ትራንስፖርት፣ የመንገድ መርበብ፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ የቤቶችና የማኅበራዊ አገልግሎቶች፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ ማኅበራዊ አገልግሎቶች፣ የሕንፃ ከፍታ፣ የታሪካዊ ግንባታዎችና ሥፍራዎች፣ ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የኢኮኖሚ ልማት ፕላን፣ የከተማ መዋቅርና ዕድገት፣ መሬት አጠቃቀም፣ መልካም አስተዳደርና የከተማ ፋይናንስ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የአካባቢ ልማት ፕላን፣ አቅም ግንባታ ይገኙበታል፡፡

‹‹ማስተር ፕላን›› ወይም ‹‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን›› በቅርቡ ከፍተኛ ውዝግብ ማስነሳቱ እና ለተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እና ብጥብጥ መነሻ ሆኖ የህይወትና ንብረት ጥፋት ማስከተሉ ይታወሳል፡፡

የዕቅዱም ዕጣ-ፈንታ ያልለየለት ስለሚመስል ለተመራማሪዎች እና ተንታኞች ሊጠቅም ስለሚችል ሰነዱን አትመነዋል፡፡

ሰነዱን ዳውንሎድ ለማድረግ ይህን ይጫኑ፡፡(link) – 7 MB

የኢንተርኔት ኮኔክሽንዎ ደካማ ከሆነ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ [2.5 MB]