(ክንፉ አሰፋ)

ከምርጫው ጥቂት አስቀድሞ የወርቅነህ ገበየሁ አያት ስም ወልደኪዳን ነበር። የቀድሞ ወዳጄ ወርቅነህ የአያቱን ስም ከወልደኪዳን ወደ ነገዎ ለመቀየር የወሰደበት ግዜ እና ምክንያቱ አላስደነቀኝም። ይህንን የዘር ፖለቲካ ጨዋታ ጠንቅቆ የሚያውቀው ዶ/ር መረራ ጉዲናም የተቃዋሚ እጩ ተመራጭ ነበር።

ከወራት በኋላ ወርቅነህ የደህንነት ሃላፊ ሆኖ ሻሸመኔ ስራ መጀመሩን ሰማሁ። ይህንን ዜና ሰምተን ብዙ ሳንቆይ “ወርቅነህ በጦር መሳሪያ ሽያጭ ተያዘ” ተብሎ ወደ እስር ቤት ተወረወረ።
ከሰባት ወራት በኋላ ወርቅነህ ገበየሁ ከእስራት መፈታቱን ሰማሁ። ከእስራት ሲፈታ ግን የምናውቀው የወርቅነህ ገበየሁ የዘር ሃረግ ተቀይሮ፤ የ‘ኦሮሞ’ ብሄር ተወላጅ ተብሎ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ከፍተኛ አመራር ሆኖ፤ ሹመት አግኝቶ የኢህአዴግን ካምፕ በግላጭ ተቀላቀለ… ወጣት ወርቅነህ ገበየሁ።
የእድሜ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ፣ በተለይ በፖሊስ ሰራዊት ስራ የሚጠይቀው የስራው ስነ-ስርዓት እና በሙያው ስነምግባር ላልተካነ ግለሰብ ያንን ትልቅ ስፍራ እንዲመራ ነው፤ አቶ መለስ ዜናዊ ሹመት የሰጡት።
አንዳንዴ ወርቅነህ ገበየሁ በቴሌቭዥን ሲቀርብ የድሮውን መልካም ሆነ ክፉ ነገር እያሰብኩ፤ “ወይ ጊዜ” ማለቴ አልቀረም። ወርቅነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ በባችለር ዲግሪ በጥሩ ውጤት የተመረቀ ወጣት ስለሆነ ከሌሎቹ ፊደል ካልቆጠሩ የህወሃት ባለስልጣናት የተሻለ ነው። ሆኖም በማናቸውም ጊዜ የግል ፋይላቸው ታይቶ ወደ እስር ቤት ሊወረወሩ ከሚችሉት፤ በ“ቀይ መስመር” ከቆሙት ባለስልጣኖች አንደኛው መሆኑ እርግጥ ነው። ግና ለጌቶቹ ታማኝ መሆኑን በዘሩ ብቻ ሳይሆን በስራውም አረጋግጦላቸዋል። ዛሬ ኦህዴድን የሚመራው የኦሮሞ ተወላጅ ሳይሆን የኦሮሞ ተናጋሪ ትግሬ እንዲሆን የተፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ትክክለኝስዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ህወሃት እምነት ስላጣ ይመስላል።

Source: ኦህዴድን የሚመራው ኦሮሞ ሳይሆን ኦሮምኛ ተናጋሪ ትግሬ ነው