FOR BETTER OROMIA

የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ተከበረ

የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በደማቅ ስነ ስርዓት ተከበረ።

Irreechaa 2015ይህ ከብረ በዓል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ትኩረት ከተሰጣቸው ህዝባዊ በዓላት አንዱ ነው።

ኢሬቻ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት መገለጫ ከሆኑት ወስጥ አንዱ ሲሆን፥ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች በስፋት የሚከበር የባህልና እሴት መገለጫ የምስጋና በዓል ነው።

የክልሉ መንግስትም ይህንን ህዝባዊ በዓል ጠብቆ ለማቆየትና ህብረተሰቡም የራሱን እሴት እንዲጠብቅና ለመጪው ትውልድ እንዲያስተላልፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራሁ ነው ብሏል።

በዚሀም ባህላችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ተከብሯል።

በዓሉ ትናንት በተለያዩ ሲምፖዚየምና ፌስቲቫሎች የተከበረ ሲሆን፥ በዛሬው እለት በሆራ አርሰዲ በገዳ አባቶች ምስጋናና ምርቃት ተካሂዶ የበዓሉ ፍጸሜ ሆኗል።

በዓመት ሁለት ጊዜ ማለትም የቱሉ ወይም የተራራና በመልካ የሚከበረዉ የኢሬቻ በአል የመስከረም መባቻው በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብሯል።

– See more at: http://www.fanabc.com/index.php/news/item/10675-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%88%AC%E1%89%BB-%E1%89%A0%E1%8B%93%E1%88%8D-%E1%89%A0%E1%89%A2%E1%88%BE%E1%8D%8D%E1%89%B1-%E1%88%86%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%88%B0%E1%8B%B2-%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%89%A0%E1%88%A8.html#sthash.Oyy9Ib0O.dpuf